15 Free YouTube subscribers for your channel
Get Free YouTube Subscribers, Views and Likes

የኢዩ ጩፋ የሐሰት ትንቢት (Eyu Chufa's false prophecy)

Follow
Zelalem Mengistu

ይህን የማካፍለው ለማስጠንቀቅ ነው። አስተዋይ ይጠንቀቅ።

ኢዩ ጨፋ ይባላል። ከዚህ በፊት አንድ ሁለት የራሱን የተለጠፉ ቪድዮዎች በማቅረብ ከቃሉ ጋር ገልጨው ነበር። አንዴ በጉባኤ እግር ሲያስረዝም ነበር ያቀረብኩት። ሌላ ጊዜ ገንዘብ ሲያባዛ ከሚያሳይ ምስል ጋር አቅርቤው ነበር። ገንዘብ ሲፈጥር፤ መፍጠርም ያምራቸዋል። እግር ማስረዘሙ ድራማ ነው። አንድ እግሩ ያጠረ ሰው እያነከሰ ቀርቦ አይደለም ተፈውሶ ወይም ተአምር ሆኖ ሁለት እኩል እግሮች ኖረውት ጌታን እያመሰገነ የወጣው። እዚያ መድረክ ላይ የሆኑ ቁመታቸው ያጠረና መርዘም የሚፈልጉ ሙጫዎች ኮልኩሎ ነው ያፌዘው። እንዲህ ያለውን ቅሌት ሊራንሶም፥ የዳንሳ ሞግዚት ሀብታሙም አድርገዋል። እንዲህ ያለ ዝተታም ቀልድ በጌታ ስም መደረጉ አሳፋሪ ነው። ጩፋ ገንዘብ ማባዛቱ ደግሞ እውነት ገንዘቡ አልበዛም እንጂ በዝቶ ከሆነ ተአምር ሳይሆን ወንጀል ነው። ብሔራዊ ባንክ ያላተመው የተጭበረበረ ወይም ፎርጅድ ብር እኮ ነው የተመረተው። ይህ በመንግሥት አስቀፍድዶ የሚያሳስርና የሚያስቀጣ የሌብነትና የማጭበርበር ወንጀል ነው። ውሸት መሆኑን የሚገልጠው ሌላ ቀልድ ደግሞ እዚያው ገንዘብ ያባዛበት ቪድዮ ላይ ሕንጻ የምንሠራበት መሬት ልንገዛ አራት ሚሊየን ብር ያስፈልገናልና በዚህ አካውንት ቁጥር ላኩ የሚል ማስታወቂያው ነው። ያንን ከፈጠረ ይህኛውን እንዳይፈጥር ምን ከለከለው? ገንዘብ ማባዛት ሌላ የተሽሞነሞነም፥ ያልተሽሞነሞነም ስም አያስፈልገውም፤ ሌብነትና አጭበርባሪነት ነው።

ይህ ሐሰተኛ ነቢይ አምና በ2010 ለአንድ ሰው ትንበያ ተናግሮ ነበር። ትንበያው የተነገረለት ይህ ሰው፥ ሰው ሁሉ እያየ ምርኮው እንደሚመለስ፥ የፈረሰ ትዳሩ እንደሚታደስ፥ በወለዱት አንድ ልጃቸው ላይ ሌሎች አራት ልጆች ከሚስቱ እንደሚወልድና በጠቅላላ አምስት ልጆች እንደሚኖሩት፥ መጀመሪያ የምትወለደውን ልጅ እንዲያውም ከነጾታና ስሟ ተናግሯል፤ ፎቅና መኪና እንደሚሰጠው፥ በምድራዊ ነገር እንደሚባረክ፥ እንደማይሞት ነው የነገረው።


የትንበያውን ቪድዮ እንይ። . . . .

posted by saharakitexb